በዓለም ላይ ሃገር ተብለው ሰንደቅ የሚያውለበልቡ ሁሉ የሃገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሰላይና ተሰላይ (የሰላይ ተሰላይ) ማሰማራታችው ያለና የሚኖር ነው። ወያኔ የሃገር አለቃ ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እእላፍ ነዋይና የሰው ጉልበት የሚያፈሰው በሃገር ውስጥና በዉጭ ያሉ ተቀናቃኝ ሃይሎችን አሜን ለማሰኘት ወይንም ጸጥ ለማረግ በመጣር ላይ ነው። ለዚህም በበረሃ እያለ ከሶሪያ፤ከሊቢያ፤ ከኢራቅና ከአለቃው ከሻቢያ የቆነጣጠበውን ዘይቤ በሙጫ አያይዞ ሲጠቀምበት ቆይቷዋል። በሚኒሊክ ቤተመንግስት ራሱን አጠግቶ የኤርትራን ነፃነት እወቁልኝ ብሎ ለዓለም ከለፈፈ ጀምሮ ደግሞ በእንግሊዙ ኤምአይ አምስት፤ በእስራኤሉ ሞሳድና በአሜሪካው ሲአኤ ልምድና መሳሪያ እየተደገፈ የህዝባችንን መከራ አባብሶታል።
ቂጣና ቆሎ በልቶ አዳሪ የሆነውን ህዝባችንን የሚያዋክቡበት በልሃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቀ በመሄድ ላይ ነው። የስለላ መረባቸው የተዘረጋው በገጠር፤ በከተማ፤ በስደተኞች ካምፕ፤ በወታደራዊ ከፍሎች፤ በመንግስትና በግል መስራቤቶች በቡና ቤቶችና ሃበሻ በሰፈረባቸው የሰሜን አሜሪካ፤ እስያ፤ አውሮጳ፤ አረብ ሃገራትና በአውስትራሊያ ነው። ለእኛ ካላደረ ያዝና ጥለፈው የሚለው ይህ የወያኔ የስለላ መረብ የሚጠልፈው ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ነጻነት ድምጻቸውን የሚያሰሙትን ሁሉ ነው። በብቀላና በምን አለብኝ ዘይቤ አይኑ የታወረው የዚህ ጠባብ ብሔርተኛ ድርጅት አሰራር ጥፍር አርጎ የሚገዛው ለስራዓቱ ያጎነበሱትንም ሁሉ ነው።
እስቲ ወያኔ ከሚጠቀምባቸው የአፈና፤ የግድያ፤ የጠለፋ ዘዴዎች ጥቂቶችን እንመልከት።
ጠለፋ – ይህ አሰራር ማንም ቢሆን የማያውቀው ተጠላፊው በትግራይ በረሃዎች ከጭቃ በተለሰኑ ቤቶች ተወሽቆ ፍጽም የሚረሳበት አሰራር ነው። አያሌ ኢትዮጵያዊን በዚህ ሁኔታ ተወስደው የገብቡበት አይታወቅም።
ጊዜአዊ ጠለፋና ምርመራ – በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች በውጭ እጅ በሰለጠኑ የወያኔ አፋኝ ቡድን በመያዝ ምርመራ ከተደረገ በህዋላ ደስ ያላቸውን እዛው ይረሽናሉ የቀሩትን ወህኒ ያወርዳሉ – ይህ አሰራር በአዲስ አበባ አካባቢ የተለመደ ነው። ስውር እስር ቤቶች በየስፍራው ተመቻችተዋል። ይህኑ በተመለከተ የግንቦት ሰባት ዘገባን ይመልከቱ።
ቀን ቆጥሮ የሚገል መርዝ ማላስ – ይህን አስራር ለማስፈጸም በምግብ ቤቶች፤ በቡና ቤቶችና ምግብና መጠጥ በሚሽጥባቸው ስፍራዎች በተሰገሰጉ የወያኔ ሰላዮች አማካኝነት ይፈጸማል። ለዚህም ስራ መልከ መልካሞች፤ ወንድን ማባብል የሚያውቁበት ተመርጠው ስትራቴጂክ በሆነ ስፍራዎች የመደባሉ። የወያኔን ትዕዛዝ ያዳምጣሉ፤ ይፈጽማሉ። ይህ አሰራር የስደተኛ ካምፓችን ሁሉ ያጠቃልላል።
የቡድን ደብደባ – ይህ ወያኔ የተካነበት የቆዬ ብልሃቱ ነው። የአለም አጫዋቹና ለወያኔ ስርዓት አዳሪውን ሰለሞን ተካልኝን አማኝ ነኝ ብሎ ወደሃገር ከገባ በህዋላ ተሰብስበው የመቱት አለቅነታቸውን ለማሳወቅ ነው። በዚህ ተግባር ላይ ያሰማራው የትግራይ ተወላጆችን ድላ አስይዞ ሲያስደበድብ የቆየ ሲሆን አሁን ከሆነ ደግሞ ስራ ፈትና የከተማ ወንጀለኞችን መጠቀም ጀምረዋል።
የግድያ ውሳኔ – ይህ አፈጻጽም ብዙ ዘይቤ ይከተላል። በመኪና ገጭቶ በመግደል አፈትልኮ መጥፋት፤ መውጫ መግቢያውን አፍኖ በመያዝ ግድሎ መሰወር ወይም አስከሬኑን አንስቶ በአምቡላንስ መውሰድና ከሙታን ማረፊያ መጨመር፤ አታሎ ከከተማ ውጭ በማውጣት በአዘጋጃቸው የቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ማስገደል። የካፒቴን ዳንኤል በየነ ድከም ላይ አገዳደል ይህን የወያኔ አሰራር አጉልቶ ያሳያል። በመዝናኛና በፓለቲካ ስብሰባዎች ላይ ጠብ እንዲነሳ በማረግ በግርግር መካከል ያልተፈለጉ ሰዎችን በታጣቂዎች ማስገደልና ዜናውን አጣሞ ማናፈስ። በተጠርጣሪው የመኖሪያ ቤት በድንገት በመድረስ በገመድ አንጠልጥሎ በመግደል ራስን እንደገደለ አስመስሎ ማቅረብ (የገንዘብ ስርቆትን ለማቆም የታገሉ የባንክ አመራር በዚህ መንገድ ነው የተገደሉት) ወያኔ ከሚገለገለባቸው ዜዴዎች ጎልተው የሚታዩት ናችው።
ወያኔ በቂም የሰከረ ድርጅት ነው። ለወያኔ አማራ ሁሉ ጠላቱ ነው። ሞቶ መነሳት በተሰኘው የህይወቱ ስንክ-ሳር ካፕቴን ተሾመ ተንኮሉ በወያኔ እጅ የደረሰበትን ግፍና እናቱ እርሱን ለመፈለግ የወያኔ አለቆች ደጅ የጠኑበትን ሁኔታ ሳነብ መቃብር ከገባች ዘመን የተቆጠራት ውድ እናቴ እኔኑ ከስር ለመጠየቅ መጥታ የተንጋላታችው ትዝ ብሎኝ ስቅስቅ ብየ ነበር ያነባሁት። የማያልፍላት ሃገር። ግፈኞች የሚናጠቋት ምድር። ታሪክን ቀዶ መጻፍና ቆርጦ መቀጠልን የተካኑት ወያኔዎች ህዝባችንን አህያ ጅብ በላ እያሉ ያሞኙታል።
ይህ ድርጀት አሰራሩ እንደ ኢጣሊያኑ የማፍያ ቡድን ነው። ለመኖር ትገላለህ፡ ለቡድኑ ጠቀሜታ አላስፈላጊ ወይም የዓይን ምስክር መሆንህ ሲያስፈራቸው አንተንም አፈር ይመልሱብሃል። ከዚያ ቁጣ አምልጠው በስካንድኔቪያና በሌሎች የአለማችን ክፍል ተደብቀው የሚኖሩ አሉ። በአፈናና ግድያ እድሜን ማራዝም እንጂ ህዝብ ያቀፈው የሰከነ ህይወት መኖር አይቻልም። ወያኔ ልብ ገዝቶ ለአንዲትና ሁሉ አቀፍ ለሆነች ኢትዮጵያ በመቆም ያፈረሰውን ማስተካከል እስካልቻለ ድረስ አወዳደቁ እንደ ሮም አወዳደቅ ነው የሚሆነው። የማስብ፤ የመናገር፤ የመጻፍና የመሰብሰብ ነጻነት ለህዝባችን በመስጠት ዘረኛነቱን ከራሱ ላይ እስካላወለቀ ድረስ ወያኔ በነፋስ እንደተነሳ የበረሃ አሽዋ መበተኑ አይቀርም።
Wednesday, January 26, 2011
የወያኔ የስለላ መረብና የአፈና ዘዴዎች — አደፍርስ ተሰማ
Posted by prayethiopia1 at 10:31 PM
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
0 comments:
Post a Comment